NCB/PFSA6/RDF- 2012/LR/02/19
June 29, 2019
Tender Code: NCB/PFSA6/RDF- 2012/LR/02/19
Tender Type: NCB
Closed Date: 07/15/2019 2:00pm
Opening Date: 07/15/2019 2:30pm
Product category: chemicals
Download File: Download
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
የመድሐኒት አቅርቦት ኤጀንሲ /መአኤ/
ከሀገር ውስጥ አምራቾች የህክምና ላብራቶሪ ኬሚካሎች ለመግዛት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው ቁጥር፡- NCB/PFSA6/RDF- 2012/LR/02/19
በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ የሀገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች ከኢትዮጵያ የምግብ የመድሐኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣንን የማምረቻ ፈቃድ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባችዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የማይመለስ ብር 300 መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸው ዋናውንና ሁለት ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ስምና አድራሻ እንዲሁም አስፈላጊ መረጃዎች በመጻፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ ከታች በተገለፀው አድራሻ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ይሸጥና የመዝጊያው ሰዓት ከቀኑ 8፡00 ሲሆን የጨረታው መክፈቻ በተመሳሳይ ቀን 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- በመጫረቻው ሰነድ ላይ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች 500,000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ ከኢንሹራንስ ተቋም ያልሆነ ወይም በምክንያት ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional bank guarantee) ወይም በሲፒኦ(CPO) በመጫረቻ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መጠን መሰረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የመገምገሚያ መስፈርቱም በዝርዝር በመጫረቻ ሰነዱ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
- ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተካተቱ ሕጎች በሀገራዊ ግዥ መመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡
አድራሻ፡– የመድሐኒት አቅርቦት ኤጀንሲ /መአኤ/ የጨረታ አስተዳደር ዳይሬክሬት ከጳውሎስ ሆስፒታል ፊት ለፊት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የፖስታ ሣጥን ቁጥር 21904
የስልክ ቁጥር +251 11 276 63 27 ፋክስ +251 11 275 25 55 አዲስ አበባ
የመጫረቻ ሰነዱን ከላይ በተገለፀው አድራሻ ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ጠዋት እና ከ7፡30-11፡30 ከሰዓት በኋላ መግዛት ይቻላል፡፡
የመድሐኒት አቅርቦት ኤጀንሲ( መአኤ)